በሞተር ሥራ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምረትስ ለመምጣት አስፈላጊ መስፈርቶች

ጊዜው ያላለፈበት ከሰድስት ወር በላይ ያለው ፓስፖርት ያስፈልጋል በምያመለክቱበት ወቅት የፓስፖርቱን የውስጥ ክፍል ፎቶ ስምና ለሎች ምረጃዎች ያሉበትን ክፍል በጥራት Scan ተደርጎ PDF ወይም JPG ፋይል መጫን ይኖርቦታል።

ፓስፖርት
በቅርብ ጊዜ የተነሱት ጥራት ያለው ፕሮፈሽናል (የስቱዲዮ) ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ባክግራውንዱ ምንም ዓይነት ነገር የለለው ባዶ ነጭ ሆኖ የለበሱት ልብስ ለላ ቀለም ብሆን ይመረጣል ፎቶው JPG እና ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት።

ጉርድ ፎቶ
ከወንጀል ነጻ የሚል በአካባቢያችሁ ከሚገኝ የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት አንድ ማዕከል አሻራችሁን ሰጥታችሁ የሚስጣችሁን ኦሪጂናል ደብዳቤ በቴሌ ሳይን አፕልከሽን አማካይነት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስተር በመላክ እንዲረጋገጥ አድርጋችሁ ያንን ደብዳቤ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምረቶች ኤምባስ ስይስተም ላይ ማያያዝ ይኖርቦታል።

ከወንጀል ነጻ ደብዳቤ
በሞተር ሥራ ለመምጣት ስያስቡ አስቀድመው ሞተር መንዳት መቻል ይኖርቦታል እንዲሁም እንጊልዘኛ ባይችሉ እንኳን መሠረታዊ የሚባሉ መግባቢያዎችን መቻል አለቦት ይህንንም የሚያሳይ ከአንድ ደቂቃ ያልበለጥ አጭር ቭድዮ ሞተር እየነዱ እንዲሁም በእንጊልዘኛ እራሶን እያስተዋወቁ ቭድዮ ቀርጸው መላክ ይኖርቦታል።

አስፈላጊ ችሎታዎች
በምትመጡብት የሥራ ዘርፍ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚሰጠውን ስልጠና መቀበል እና ሲኦሲ መፈተን ግድ ባይሆንም እንደሁነታው አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
